የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ስም ዝርዝር
ይፋ ሆነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የ1ኛ ዙር የመሬት ሊዝ
ጨረታ አሸናፊዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
በቢሮው የለማ መሬት ማስተላለፍ ቡድን አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ፣ በከተማዋ ላለፉት አምስት ዓመታት ቆሞ የነበረውን መሬትን በሊዝ ጨረታ የማስተላለፍ ተግባር ዳግም መጀመሩን አስታውሰው፣ ከግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በይፋ ተከፍቶ አሸናፊዎቹ የተለየው የ1ኛው ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ አሸናፊዎች ስም ዝርዝር ይፋ መደረጉን ነግረውናል፡፡ በዚህ ጨረታ ዝቅተኛ ዋጋ የተመዘገበው በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲሆን፣ ይህም በካሬ ሜትር 20 ሺህ ብር ነው፡፡ ከፍተኛው በአራዳ ክፍለ ከተማ መሆኑን ጠቁመው፣ በካሬ ሜትር 414 ሺህ ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ለ21 ሺህ 636 ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ መሸጡን ጠቅሰው፣ ከእነዚህ ውስጥ 11 ሺህ 457 ሰነዶች ተሞልተው ሳጥን ውስጥ ገብተዋል ብለዋል፡፡